Posts

Showing posts from December, 2021

ካንሰር/Cancer

 #ካንሰር • ካንሰር ማለት በሰውነታችን ውስጥ ጥቅም የማይሰጡ እና ባልተለመደ መንገድ ሰውነትን የሚያራቁቱ እንጭጪ ያልበለፀጉ ህዋሳት ወይም ሴሎች ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መልኩ ሲመረቱና ሲያድጉ ነው። • እነዚህ የማይጠቅሙና ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ህዋሳት በብዙ ቢሊዮን ወይም ሚሊዮን ከዚያም በላይ ሲሆኑ የጤነኛውን ህዋስ ወይም ሴል አየር፡ ምግብ፡ ውሀና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በመጋራት ሰውነትን በማራቆት ለበሽታና ችግር አሳልፈው ይሰጣሉ። • ከ200 በላይ የሚሆኑ የካንሰር አይነቶች አሉ። ለምሳሌ የቆዳ፡ የሳንባ፡ የጡት፡ የፊንጢጣ አካባቢ፡ የአጥንት ካንሰርና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። • ካንሰር ሴሎች በአብዛኸኛው በአንድ ቦታ ላይ የሚጠራቀምና አጢ መሳይ እድገት ሲኖረው ቀሪው ደግሞ በደምና በሌሎች የሰውነት ፈሳሽ ማዘዋወሪያ ቱቦዎች በኩል በመላ ሰውነት የሚሰራጭና ሰውነትን የሚያጠቃ ነው። • በጣም የተለመዱት የካንሰር አይነቶች የቆዳ፡ የሳንባ፡ የጡት፡ የማህፀን፡ የሆድና አንጀትፊንጢጣ አካባቢ፡ የደምና ጉበት እንድሁም የጣፊያ ሲሆን በአለም ላይ 8.2 ሚሊዮን ሰዎች በአመት እንድሞቱ ምክናየት ይሆናል። ይህ ቁጥር በ2030 ወደ 13.1 ሚሊዮን ከፍ ይላል ተብሎ ይታሰባል። #የካንሰር ምክናየቶችና አጋላጭ ነገሮች • የብዙዎቹ ካንሰር ምክንያት አይታወቅም። ነገር ግን የሚከተሉት እንደ አነሳሽ ወይም አጋላጭነት ይቆጠራሉ። 1. ጥቁር ወይም ነጭ ሰው መሆን። ለምሳሌ የቆዳ ካንሰር ነጮችን ይበልጥ ያጠቃል። 2. ለኬሚካልና መርዛማ ነገሮች ተጋላጭ መሆን 3. ለተለያዩ ጨረሮች መጋለጥና መጠቃት 4. በቤተሰብ ወይም ዘር 5. በሽታ ተከላካይ ሴሎች አደገኛ መሆንና የራሱን አካል ማጥቃቱ 6. ዉፍረት 7. የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ 8. በፋብሪካ የታሸጉ ምግቦች ተጠቃሚ መሆን 9...

Stroke... በተለምዶ መገኛ

Stroke... በተለምዶ መገኛ ☠ሁለት አይነት ሊሆን ይችላል ፩; ወደ ጭንቅላት የሚሄድ ደም መቋረጥ(Ischaemic stroke) ፪;ጥንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ hemorrhagic stroke) 🏹 በምን ምክንያት ሊመጣ ይችላል?? ፩;መቆጣጠር የምንችላቸው(modifiable risk factor √የደም ግፊት √የስኳር ህመም √የልብ ህመም √የሰውነት የስብ መጠን መብዛት √ሲጋራ ማጨስ √አልኮል መጠጣት ፪;መቆጣጠረ የማንችላቸው(Non_modifiable risk factor( √እድሜ"እርጅና" √በቤተሰብ የሴትሮክ ታማሚ መኖር ✍ ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?(Symptoms) √ከፍተኛ የሆነ እራስ ምታት √ማስታወክ √የሰውነት አካላት መስነፍ √የፊት መጣመም √ሽንት አና ሰገራ መቆጣጠር አለመቻል √የንቃተ ህሊና መቀነስ √ማውራት አለመቻል ወይም መኮላተፍ 🏹💣 ስትሮክን እንዴት እንከላከላለን:(Prevention method) 🚭 ሲጋራ ማጨስ ማቆም 🍺 የአልኮል መጠጥ መቀነስ 🛑 የደም ግፊትና ኮሌስትሮል መጠንን ማስተካከል ✅ ስኳር ህምን ባግባቡ መቆጣጠር 🏋🏾‍♀‍ ቦርጭና ክብደትን ማስተካከል 🍏 ጤናማ አመጋገብ 🏃🏾‍♂‍ በቀን ለ30ደቂቃ ያክል እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ NB;እባክው የቡና ወሬ አቁመው የሀኪምውን ምክር ይሰው!!! ዶ/ር ካሳዬ ደመቀ (የድንገተኛ እና ፅኑ ህክምና ስፔሻሊስት)

ማዬማ(Myoma

ማዬማ(Myoma ማዬማ(Myoma) ምንድን ነው?የማሕፀን ፋይብሮይድስ ብዙውን ጊዜ ልጅ በሚወልዱባቸው ዓመታት ውስጥ የሚታየው የማኅጸን ዕጢ ሲሆኑ ነቀርሳ ያልሆኑ እድገቶች ናቸው። ሊዮዮሞማ ወይም ማዮማ ተብሎም ይጠራል ፣ የማሕፀን ፋይብሮይድስ ከማኅፀን ካንሰር የመጋለጥ እድሉ ጋር የተቆራኘ አይደለም እና በጭራሽ ወደ ካንሰር አያድግም። የፋይብሮይድስ መጠን ፣ በሰው ዓይን ሊታይ ከማይችል እስከ ማህፀንን ሊያዛባ እና ሊያሰፋ የሚችል ግዙፍ እና ብዙ ሊሆን ይችላል። አንድ ፋይብሮይድ ወይም ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ። በጣም ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ፣ በርካታ ፋይብሮይድስ ማህፀኑን በጣም ስለሚያሰፋ የጎድን አጥንት እስኪደርስ እና ክብደትን ሊጨምር ይችላል። ብዙ ሴቶች በሕይወታቸው ውስጥ አንዳንድ ጊዜ የማሕፀን ፋይብሮይድ አላቸው። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ምንም ምልክት ስለማያሳይ የማሕፀን ፋይብሮይድስ እንዳለዎት ላያውቁ ይችላሉ። በማህፀን ምርመራ ወይም ቅድመ ወሊድ አልትራሳውንድ ወቅት ሐኪምዎ በአጋጣሚ ፋይብሮይድስ ሊያገኝ ይችላል። ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው? ብዙ ፋይብሮይድ ያለባቸው ሴቶች ምንም ምልክቶች የላቸውም። በሚያደርጉት ውስጥ ምልክቶቹም እንደ አቀማመጥ፣ መጠን እና ብዛት ይለያያሉ። ምልክቶች ባላቸው ሴቶች ውስጥ የማሕፀን ፋይብሮይድስ በጣም የተለመዱ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው:- - ከባድ የወር አበባ መፍሰስ  - የወር አበባ ቀናት መራዝም(ከ7 በላይ) - የደረት ግፊት ወይም ህመም  - ተደጋጋሚ ሽንት ሽንት ማለት - ሆድ ድርቀት  - የጀርባ ህመም ወይም የእግር ህመም ፋይብሮይድስ በአጠቃላይ በማህፀን አቀማመጥ በ3 ይመደባሉ።  ማዬማ ምን ችግር ሊያስከትል ይችላል? የማኅጸን ፋይብሮይድስ አብዛኛውን ጊዜ አደገኛ ባይሆንም አንዳንዴ፣ - ከባድ የደ...

የኮሶ ትል

 #የኮሶ ትል • የኮሶ ትል በዋናነት አንጀትን የሚያጠቃ ትላትል ነው። ከአጀት ውጭ ወደተለያየ የሰውነት ክፍልም ሊሰራጭ ይችላል።  አንድ ሰው የኮሶ ትል አለበት የሚባለው በአንጀት ውስጥ የኮሶ ትል መኖሩ ሲረጋገጥ ነው። ያደገ የኮሶ ትል እስከ 80 ጫማ ወይም 25 ሜትር ያህል ቁመት ሲኖረው በእድሜም በሰውነት ውስጥ እስከ 30 አመት ሊቆይ ይችላል። • የኮሶ ትል እጭ ወይም ጉልምስ ከምግብና ውሀ ጋር በመቀላቀል በአፍ በኩል ወደ ሰውነት ይገባል። እጩ ወይም ጉልምሱ ከተወሰነ ጊዜ በሗላ ወደ ሙሉ አዋቂ ትልነት ይቀየራል።  እጩ ወይም ጉልምሱ ከአንጀት በተጨመሪ በሌላ የሰውነት ክፍል ላይም ሊኖርና ሊሰራጭ ይችላል። • የኮሶ ትል እራስ፡ አንገትና የተከፋፈለ የሰውነት ክፍል አለው። እራሱን ከአንጀት ግድግዳ ጋር ያጣብቅና በሰውነት አካሉ እንቁላሉን በመፍጠር ያሳድጋል። • በኮሶ ትል የሚመጣ ኢንፌክሽን ብዙ ጊዜ ቀለል ያለ ኢንፌክሽን ነው። በተለይ የትሎቹ ብዛት ከሁለት ካልበለጠ ነው። የትሉ ብዛት ከሁለት በላይ ከበለጠ ህመሙ ሊከብድ ይችላል። #የኮሶትል_ምልክት • አብዛኸኛው ሰው ምልክት አያሳይም። ቀሪዎቹም ቢሆኑ በኮሶ ትሉ አይነትና በተቀመጠበት የሰውነት ክፍል ይወሰናል። #እንደ አጠቃላይ ግን • ማቅለሽለሽ • ድካም • የምግብ ፍላጎት ማነስ • የሆድ ህመም • ተቅማጥ • ድብርት • ጨው የመፈለግ ስሜት • ክብደት መቀነስ • የምግብ ልመት ችግር #እጩ ወይም ጉልምሱ ከአንጀት ውጭ ያለ የሰውነት ክፍል የሚያጠቃ ከሆነ • የራስ ምታት • እባጭ • ማሳከክ / አላርጅክ • የነርቭ ችግር በተለይ እንደሚጥል በሽታ አይነት ውስሜት ይኖራል። #ምክንያቱ • ከምግብና ውሀ ጋር የኮሶ ትል እጭ ወይም ጉልምስ ወደ ሰውነት መግባቱ ነው። #ለኮሶትል የሚያጋልጡ ነገሮች...

የደም መርጋት

 የደም መርጋት  የደም ስር ላይ ደም መርጋት የምንለው ደም በስውነታችን ውስጥ በሚገኙ የደም መልስ ስሮች ላይ መቋጠር ወይም መርጋት ሲፈጠር ማለት ነው ። ይህም በአብዛኛው የሚከሰተው በእግራችን አካባቢ በሚገኙ የደም ስሮች ላይ ነው ። ዋነኛ ምልክቶች 🔺 የእግር ማበጥ 🔺 በተጠቃው ወይም በተጎዳው የአካል ክፍል የመሞቅ ስሜት  🔺 የቆዳው ቀለም መቀየር 🔺 የህመም ስሜት መኖር መንስኤው 🔺 እድሜ ከ60 በላይ 🔺 ለረጅም ጊዜ አልጋ ላይ የተኙ ሰዎች 🔺 ከመጠን በላይ ውፍረት 🔺 ከቤተሰብ የሚመጣ 🔺 ሲጋራ ማጨስ 🔺 ለረጅም ጊዜ መቀመጥ 🔺 በሰውነት ውስጥ በቂ ፈሳሽ አለመኖር 🔺 እርግዝና 🔺 የእርግዝና መከላከያ እንክብል ለብዙ ጊዜ ማቅረብ 🔺 የሆርሞን መተካት ህክምና ከተደረገ ህክምና 🔺 ደምን ለማቅጠን የሚረዱ መድሃኒቶችን መውሰድ አንቲ ኮአጉላንት (Anti-coagulant) 🔺 ቀዶ  ህክምና መፍትሄ 🔺 ረጅም የእግር ጉዞ ማድረግ 🔺 ውሃ አብዝቶ መጠጣት 🔺 ውሃ አዘል ፍራፍሬዎችን አብዝቶ መጠቀም 🔺 የምንቀመጥበትን ሰዐት መቀነስ 🔺 በእግር ውስጥ የደም ዝውውርን ለመጨመር የሚደረጉ የሚያጣብቁ ልብሶች (ስቶኪንግ) መጠቀም

የስኳር በሽታ ክትትል

 የስኳር በሽታ ክትትል የሚፈልግ በሽታ ነው ፡ አንድ ሰው በዚህ በሽታ ከተጠቃ ህይወቱን ሙሉ ሊቆጣጠረው እና ሊከታተለው ይገባል ፡ እርስዎም በቤተሰብዎ ውስጥ የስኳር ታማሚ ካለ መድሀኒቱን በየጊዜው ተከታትሎ ከማስወሰድ ባለፈ በተቻሎት መጠን ስለ በሽታው በማወቅ ታካሚውን ሊረዱት ይችላሉ ፡ ለጅማሬ ያክል ፡- 1. አመጋገብ - የተመጣጠነ ምግብ መብላት ታማሚው ክብደት እንዳይቀንስ ከማገዝ ባለፈ አንዳንድ ኬዞች ላይ ኢኔሱሊንን ሲተካ ያሳያል ፡ በተጨማሪም ምግቦች ሁሌም በተመሳሳይ ሰአት እንዲቀርቡ ማድረግ እና እንደ ሀኪሙ ትእዛዝ ክምግብ በፊት የጉሉኮስ መጠን መለካት አስፈላጊ ነው ። 2. የስፓርት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ማውጣት - ስፖርት ለታማሚው በደሙ ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር እና ክብደት እንዳይጨምር ይረዳል ፡ በቀን ለ30 ደቂቃ ቤት ውስጥ ዎክ ከማድረግ ጀምሮ ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ከበቂ ፈሳሽ እና ምግብ ጋር ታግዞ ማድረግ ጥሩ ነው ። 3. የእግር ጥንቃቄ - የስኳር በሽታ በእግር ውስጥ የሚገኙ ነርቮችን የማጥቃት ባህሪ አለው ፡ ከዛም የሚብሰው ታማሚው ምንም አይነት ህመም ወይም ምልክት ሳያይ የሚባባሰው ነገር ነው ፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በተደጋጋሚ የታካሚን እግር ቁስል ወይም ከለር ቼክ ማድረግ ፡ የታካሚን እግር ሁሌም ንፁህ እና ደረቅ ማድረግ ፡ ታካሚ ለቼክ አፕ ሲሄድ ሁሌም እግሩ እንዲታይ ማድረግ የተወሰኑት ናቸው ። 4. የደም ስኳር ማነስ (Hypoglycemia) - አንዱ የስኳር በሽታ አደገኛ ውጤት የደም ስኳር ማነስ (Hypoglycemia) ነው ፡ ይህን ችግር ተከታትለው ካልደረሱበት ታማሚው ራሱን ሊስት ወይም ሊያንቀጠቅጠው ይችላል ፡ የደም ስኳር ማነስ (Hypoglycemia) ምልክቶች ውስጥ መርበትበት ፣ ግራ መጋባት ፣ ማላብ ፣...

ሾተላይ ምንድን ነው?

 ሾተላይ ምንድን ነው? 🗡️😮 ብዙ ጊዜ አንዲት እናት ከመጀመሪያ እርግዝናዋ በኃላ በተደጋጋሚ የሚከሰት የጽንሱ መጥፋት(በማህፀን ዉስጥ መሞት) ነው። ይህ ለምን ይሆናል? 🤔 በምን ምክንያትስ ይከሰታል ⁉️ 🔷 ስለ ሾተላይ ለመረዳት በመጀመሪያ ስለ ደም አይነቶች ማወቅ ይኖርብናል :: ❤️ የሰዎች ደም አይነት በአራት መደብ ይከፈላል(A, B, AB, O) ❤️ እነዚህ ደግሞ እያንዳንዳቸው በሁለት አበይት መደብ ይከፈላሉ::   ይሄም ፖዘቲቭ እና  ኔጋቲቭ እንለዋለን:: በትክክለኛ አጠራሩ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) እና አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +)ይባላል 🔷ለምሳሌ፦ የአንድ ሰው የደም ዓይነት A+ ወይም A- ሊሆን ይችላል,  B+ ወይም  B - በተመሳሳይ O+ ወይም O- ሊሆን ይቺላል :: 🤱 የሰው ማንነቱ ከእናቱና ከአባቱ በሚወስደው የዘር-መል ይወሰናል። የደም ዓይነትም በዚሁ መልክ እንወስዳለን። ከአር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) አባት እና ከአር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-) እናት የሚፈጠር ጽንስ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የመሆን እድሉ የሰፋ ነው። 🛑ሾተላይ የሚከሰተው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ  ኔጋቲቭ ሆኖ (ለምሳሌA-, B-, AB-,  O-) ሆኖ ልጇ ደሞ  ፖዘቲቭ ከሆነ (ለምሳሌ A+, B+, AB+, O+) ከሆነ እና የ ልጁ ደም ህዋስ ወደ ሰውነቷ ሲገባ ፖዘቲቭ የሆኑ የደም ህዋሶችን በሙሉ የሚያጠፋ ተዋጊ ንጥረ-ነገር (Antibodies)በደሟ ውስጥ ይመረታል።  🛑 ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ህይወቷ ፍጻሜ ድረስ ይኖራል። 🛑በመሆኑም በማህጸንዋ ውስጥ የያዘችው ልጅ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ የተመረተው ንጥረ-ነገር(antibodies) ጽንሱን እንደ ባእድ...