የደም መርጋት
የደም መርጋት
የደም ስር ላይ ደም መርጋት የምንለው ደም በስውነታችን ውስጥ በሚገኙ የደም መልስ ስሮች ላይ መቋጠር ወይም መርጋት ሲፈጠር ማለት ነው ። ይህም በአብዛኛው የሚከሰተው በእግራችን አካባቢ በሚገኙ የደም ስሮች ላይ ነው ።
ዋነኛ ምልክቶች
🔺 የእግር ማበጥ
🔺 በተጠቃው ወይም በተጎዳው የአካል ክፍል የመሞቅ ስሜት
🔺 የቆዳው ቀለም መቀየር
🔺 የህመም ስሜት መኖር
መንስኤው
🔺 እድሜ ከ60 በላይ
🔺 ለረጅም ጊዜ አልጋ ላይ የተኙ ሰዎች
🔺 ከመጠን በላይ ውፍረት
🔺 ከቤተሰብ የሚመጣ
🔺 ሲጋራ ማጨስ
🔺 ለረጅም ጊዜ መቀመጥ
🔺 በሰውነት ውስጥ በቂ ፈሳሽ አለመኖር
🔺 እርግዝና
🔺 የእርግዝና መከላከያ እንክብል ለብዙ ጊዜ ማቅረብ
🔺 የሆርሞን መተካት ህክምና ከተደረገ
ህክምና
🔺 ደምን ለማቅጠን የሚረዱ መድሃኒቶችን መውሰድ አንቲ ኮአጉላንት (Anti-coagulant)
🔺 ቀዶ ህክምና
መፍትሄ
🔺 ረጅም የእግር ጉዞ ማድረግ
🔺 ውሃ አብዝቶ መጠጣት
🔺 ውሃ አዘል ፍራፍሬዎችን አብዝቶ መጠቀም
🔺 የምንቀመጥበትን ሰዐት መቀነስ
🔺 በእግር ውስጥ የደም ዝውውርን ለመጨመር የሚደረጉ የሚያጣብቁ ልብሶች (ስቶኪንግ) መጠቀም
Comments
Post a Comment