የኮሶ ትል

 #የኮሶ ትል


• የኮሶ ትል በዋናነት አንጀትን የሚያጠቃ ትላትል ነው። ከአጀት ውጭ ወደተለያየ የሰውነት ክፍልም ሊሰራጭ ይችላል። 


አንድ ሰው የኮሶ ትል አለበት የሚባለው በአንጀት ውስጥ የኮሶ ትል መኖሩ ሲረጋገጥ ነው።


ያደገ የኮሶ ትል እስከ 80 ጫማ ወይም 25 ሜትር ያህል ቁመት ሲኖረው በእድሜም በሰውነት ውስጥ እስከ 30 አመት ሊቆይ ይችላል።


• የኮሶ ትል እጭ ወይም ጉልምስ ከምግብና ውሀ ጋር በመቀላቀል በአፍ በኩል ወደ ሰውነት ይገባል። እጩ ወይም ጉልምሱ ከተወሰነ ጊዜ በሗላ ወደ ሙሉ አዋቂ ትልነት ይቀየራል። 

እጩ ወይም ጉልምሱ ከአንጀት በተጨመሪ በሌላ የሰውነት ክፍል ላይም ሊኖርና ሊሰራጭ ይችላል።


• የኮሶ ትል እራስ፡ አንገትና የተከፋፈለ የሰውነት ክፍል አለው። እራሱን ከአንጀት ግድግዳ ጋር ያጣብቅና በሰውነት አካሉ እንቁላሉን በመፍጠር ያሳድጋል።


• በኮሶ ትል የሚመጣ ኢንፌክሽን ብዙ ጊዜ ቀለል ያለ ኢንፌክሽን ነው። በተለይ የትሎቹ ብዛት ከሁለት ካልበለጠ ነው። የትሉ ብዛት ከሁለት በላይ ከበለጠ ህመሙ ሊከብድ ይችላል።


#የኮሶትል_ምልክት

• አብዛኸኛው ሰው ምልክት አያሳይም። ቀሪዎቹም ቢሆኑ በኮሶ ትሉ አይነትና በተቀመጠበት የሰውነት ክፍል ይወሰናል።


#እንደ አጠቃላይ ግን

• ማቅለሽለሽ

• ድካም

• የምግብ ፍላጎት ማነስ

• የሆድ ህመም

• ተቅማጥ

• ድብርት

• ጨው የመፈለግ ስሜት

• ክብደት መቀነስ

• የምግብ ልመት ችግር


#እጩ ወይም ጉልምሱ ከአንጀት ውጭ ያለ የሰውነት ክፍል የሚያጠቃ ከሆነ

• የራስ ምታት

• እባጭ

• ማሳከክ / አላርጅክ

• የነርቭ ችግር በተለይ እንደሚጥል በሽታ አይነት ውስሜት ይኖራል።


#ምክንያቱ

• ከምግብና ውሀ ጋር የኮሶ ትል እጭ ወይም ጉልምስ ወደ ሰውነት መግባቱ ነው።


#ለኮሶትል የሚያጋልጡ ነገሮች

• ንፅህናን አለመጠበቅ

• ከእንስሳቶች ጋር ያለ ንክኪ

• ታዳጊ ሀገር ላይ መኖር

• ጥሬና ያልበሰለ ስጋ መብላት


#ካልታከመ

• የአንጀት መዘጋት

• የነርቭና አንጎል ተግባር መስተጓጎል

• የሰውነት አካላትን ተግባር ማስተጐጎል ያስከትላል።


#መከላከያው

• ንፅህናን መጠበቅ

• ከእንስሳት ጋር ያለን ቅርበትና ንክኪ ማስወገድ

• ከሽንት ቤት መልስ እጅን በአግባቡ መታጠብ

• ምግብን ማጠብና ማብሰል

• ውሀን አፍልቶ መጠቀም

• ጥሬ ስጋ ለመጠቀም ከተፈለገ ባያስተማምንም ቢያንስ ማቀዝቀዝ

• ስጋን ማብሰል

• የከበት፡ በግ፡ ፍየል፡አሳማና አሳ ስጋን ሳያበስሉ አለመጠቀም

Comments

Popular posts from this blog

ሾተላይ ምንድን ነው?

ካንሰር/Cancer