ሾተላይ ምንድን ነው?
ሾተላይ ምንድን ነው? 🗡️😮
ብዙ ጊዜ አንዲት እናት ከመጀመሪያ እርግዝናዋ በኃላ በተደጋጋሚ የሚከሰት የጽንሱ መጥፋት(በማህፀን ዉስጥ መሞት) ነው።
ይህ ለምን ይሆናል? 🤔
በምን ምክንያትስ ይከሰታል ⁉️
🔷 ስለ ሾተላይ ለመረዳት በመጀመሪያ ስለ ደም አይነቶች ማወቅ ይኖርብናል ::
❤️ የሰዎች ደም አይነት በአራት መደብ ይከፈላል(A, B, AB, O)
❤️ እነዚህ ደግሞ እያንዳንዳቸው በሁለት አበይት መደብ ይከፈላሉ:: ይሄም ፖዘቲቭ እና ኔጋቲቭ እንለዋለን:: በትክክለኛ አጠራሩ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) እና አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +)ይባላል
🔷ለምሳሌ፦ የአንድ ሰው የደም ዓይነት A+ ወይም A- ሊሆን ይችላል, B+ ወይም B - በተመሳሳይ O+ ወይም O- ሊሆን ይቺላል ::
🤱 የሰው ማንነቱ ከእናቱና ከአባቱ በሚወስደው የዘር-መል ይወሰናል። የደም ዓይነትም በዚሁ መልክ እንወስዳለን። ከአር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) አባት እና ከአር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-) እናት የሚፈጠር ጽንስ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የመሆን እድሉ የሰፋ ነው።
🛑ሾተላይ የሚከሰተው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ ኔጋቲቭ ሆኖ (ለምሳሌA-, B-, AB-, O-) ሆኖ ልጇ ደሞ ፖዘቲቭ ከሆነ (ለምሳሌ A+, B+, AB+, O+) ከሆነ እና የ ልጁ ደም ህዋስ ወደ ሰውነቷ ሲገባ ፖዘቲቭ የሆኑ የደም ህዋሶችን በሙሉ የሚያጠፋ ተዋጊ ንጥረ-ነገር (Antibodies)በደሟ ውስጥ ይመረታል።
🛑 ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ህይወቷ ፍጻሜ ድረስ ይኖራል።
🛑በመሆኑም በማህጸንዋ ውስጥ የያዘችው ልጅ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ የተመረተው ንጥረ-ነገር(antibodies) ጽንሱን እንደ ባእድ አካል ስለሚቆጥረው ያጠቃዋል። በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ የምትይዘው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ አስፈላጊውን ህክምና ካልተደረገላት ይሞትባታል።
🛑 የደም ዓይነቱ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ከሆነ ግን አንድ አይነት ስለሆነ እንደ ባእድ አይቆጠርም ስለዚህ ልጁም በጤና ይወለዳል።
የሾተላይ ሕክምናው አለው❓️
አዎ ሾተላይ ሕክምና አለው❗️
✔️ የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) የሆነች እናት የ እርግዝና ክትትሏ እና ሕክምናዋ በሆስፒታል ውስጥ መሆን አለበት። 🏨🏥
✔️ በደሟ ውስጥ ያለውን የንጥረ-ነገር መጠን መለካትና የጽነሷን የጉዳት መጠን በማየት ብዙ ሳይጎዳ እንዲወለድ ማድረግ።🔬
✔️ በሀገራችን በቅርቡ የተጀመረው ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እያለ ደም በመለገስ እንዲያድግና እንዲወለድ ማስቻል።
✔️ ሾተላይ ከሕክምናው ይልቅ ግን መከላከሉ በጣም ውጤታማ ነው ❗️
ሾተላይን እንዴት እንከላከለው❓️
💗 ማንኛዋም ሴት ከማርገዟ ወይም ማንኛውንም ደም ከመውሰዷ በፊት የደም ዓይነቷን ማወቅ አለባት።
💗 የወንድ አጋሯን የደም ዓይነት ማወቅ አለባት።
💗 እርግዝና አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ አጋሯ ከተፈጠረ መጀመሪያ በሚደረግላት ምርመራ (indirect coomb’s test) ተዋጊ ንጥረ-ነገሩ መመረቱ እና አለመመረቱን ይረጋገጣል።
💗 እዳይመረት የሚከላከል የሾተላይ መከላከያ(Anti-D)መድኃኒት በእርግዝና 7ተኛ ወሯ ላይ ይሰጣታል።
💗 ከወለደች በኃላ የልጇ የደም ዓይነት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ በድጋሚ መድኃኒቱ ይሰጣታል።💉💉
💗 እርግዝናው ከማህጸን ውጭ ወይም በውርጃ ቢያበቃም የሾተላይ መከላከያውን መድኃኒት መውሰድ አለባት።
Comments
Post a Comment