የስኳር በሽታ ክትትል
የስኳር በሽታ ክትትል የሚፈልግ በሽታ ነው ፡ አንድ ሰው በዚህ በሽታ ከተጠቃ ህይወቱን ሙሉ ሊቆጣጠረው እና ሊከታተለው ይገባል ፡ እርስዎም በቤተሰብዎ ውስጥ የስኳር ታማሚ ካለ መድሀኒቱን በየጊዜው ተከታትሎ ከማስወሰድ ባለፈ በተቻሎት መጠን ስለ በሽታው በማወቅ ታካሚውን ሊረዱት ይችላሉ ፡ ለጅማሬ ያክል ፡-
1. አመጋገብ - የተመጣጠነ ምግብ መብላት ታማሚው ክብደት እንዳይቀንስ ከማገዝ ባለፈ አንዳንድ ኬዞች ላይ ኢኔሱሊንን ሲተካ ያሳያል ፡ በተጨማሪም ምግቦች ሁሌም በተመሳሳይ ሰአት እንዲቀርቡ ማድረግ እና እንደ ሀኪሙ ትእዛዝ ክምግብ በፊት የጉሉኮስ መጠን መለካት አስፈላጊ ነው ።
2. የስፓርት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ማውጣት - ስፖርት ለታማሚው በደሙ ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር እና ክብደት እንዳይጨምር ይረዳል ፡ በቀን ለ30 ደቂቃ ቤት ውስጥ ዎክ ከማድረግ ጀምሮ ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ከበቂ ፈሳሽ እና ምግብ ጋር ታግዞ ማድረግ ጥሩ ነው ።
3. የእግር ጥንቃቄ - የስኳር በሽታ በእግር ውስጥ የሚገኙ ነርቮችን የማጥቃት ባህሪ አለው ፡ ከዛም የሚብሰው ታማሚው ምንም አይነት ህመም ወይም ምልክት ሳያይ የሚባባሰው ነገር ነው ፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በተደጋጋሚ የታካሚን እግር ቁስል ወይም ከለር ቼክ ማድረግ ፡ የታካሚን እግር ሁሌም ንፁህ እና ደረቅ ማድረግ ፡ ታካሚ ለቼክ አፕ ሲሄድ ሁሌም እግሩ እንዲታይ ማድረግ የተወሰኑት ናቸው ።
4. የደም ስኳር ማነስ (Hypoglycemia) - አንዱ የስኳር በሽታ አደገኛ ውጤት የደም ስኳር ማነስ (Hypoglycemia) ነው ፡ ይህን ችግር ተከታትለው ካልደረሱበት ታማሚው ራሱን ሊስት ወይም ሊያንቀጠቅጠው ይችላል ፡ የደም ስኳር ማነስ (Hypoglycemia) ምልክቶች ውስጥ መርበትበት ፣ ግራ መጋባት ፣ ማላብ ፣ ረሀብ የተወሰኑት ናቸው።
ethiopiandoctorinsider
Comments
Post a Comment