ካንሰር/Cancer
#ካንሰር • ካንሰር ማለት በሰውነታችን ውስጥ ጥቅም የማይሰጡ እና ባልተለመደ መንገድ ሰውነትን የሚያራቁቱ እንጭጪ ያልበለፀጉ ህዋሳት ወይም ሴሎች ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መልኩ ሲመረቱና ሲያድጉ ነው። • እነዚህ የማይጠቅሙና ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ህዋሳት በብዙ ቢሊዮን ወይም ሚሊዮን ከዚያም በላይ ሲሆኑ የጤነኛውን ህዋስ ወይም ሴል አየር፡ ምግብ፡ ውሀና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በመጋራት ሰውነትን በማራቆት ለበሽታና ችግር አሳልፈው ይሰጣሉ። • ከ200 በላይ የሚሆኑ የካንሰር አይነቶች አሉ። ለምሳሌ የቆዳ፡ የሳንባ፡ የጡት፡ የፊንጢጣ አካባቢ፡ የአጥንት ካንሰርና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። • ካንሰር ሴሎች በአብዛኸኛው በአንድ ቦታ ላይ የሚጠራቀምና አጢ መሳይ እድገት ሲኖረው ቀሪው ደግሞ በደምና በሌሎች የሰውነት ፈሳሽ ማዘዋወሪያ ቱቦዎች በኩል በመላ ሰውነት የሚሰራጭና ሰውነትን የሚያጠቃ ነው። • በጣም የተለመዱት የካንሰር አይነቶች የቆዳ፡ የሳንባ፡ የጡት፡ የማህፀን፡ የሆድና አንጀትፊንጢጣ አካባቢ፡ የደምና ጉበት እንድሁም የጣፊያ ሲሆን በአለም ላይ 8.2 ሚሊዮን ሰዎች በአመት እንድሞቱ ምክናየት ይሆናል። ይህ ቁጥር በ2030 ወደ 13.1 ሚሊዮን ከፍ ይላል ተብሎ ይታሰባል። #የካንሰር ምክናየቶችና አጋላጭ ነገሮች • የብዙዎቹ ካንሰር ምክንያት አይታወቅም። ነገር ግን የሚከተሉት እንደ አነሳሽ ወይም አጋላጭነት ይቆጠራሉ። 1. ጥቁር ወይም ነጭ ሰው መሆን። ለምሳሌ የቆዳ ካንሰር ነጮችን ይበልጥ ያጠቃል። 2. ለኬሚካልና መርዛማ ነገሮች ተጋላጭ መሆን 3. ለተለያዩ ጨረሮች መጋለጥና መጠቃት 4. በቤተሰብ ወይም ዘር 5. በሽታ ተከላካይ ሴሎች አደገኛ መሆንና የራሱን አካል ማጥቃቱ 6. ዉፍረት 7. የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ 8. በፋብሪካ የታሸጉ ምግቦች ተጠቃሚ መሆን 9...